ቴሌቪዥን

ቴሌቪዥን

ቴሌቪዥን የስዕል እና ድምጽ ምልክቶችን ከማሰራጫ የሚቀበል የመገናኛ ዘዴ ነው። «ቴሌ-» የሚለው ክፍል በግሪክ «ሩቅ» ማለት ቢሆን «-ቪዥን» ደግሞ ከሮማይስጥ visio /ዊዚዮ/ «ማየት» («ትርዒት») ተወስዷል። በአጠቃላይ ቴሌቪዥን ማለት ተንቀሳቃሽ ምስልን (ብዙ ጊዜ ከድምፅ ጋር) ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማስተላለፍ የሚረዳ የመልዕክት ማስራጫ መንገድ ነው። ይህ ከሆነ ዘንዳ ቴሌቪዥን ምስል መቅጃውንም ሆነ ምስል መቀበያውን መሳሪያ ሁሉ ያጠቃልላል ግን በተለምዶ ቴሌቪዥን የምንለው ምስል መቀበያውን ብቻ ነው።

  • ታሪክ

ታሪክ

1873 እ.ኤ.አ. ( 1865 ዓም) የእንግላንድ ኤንጅኔር ውሎቢ ስሚስ ባደረገው ጥረት ጥንተ ንጥሩ ሴሌኒይም ብርሃን-አስተላልፎሽ መሆኑን ገለጸ።

1884 እ.ኤ.አ. ፓውል ጎትሊብ ኒፕኮው የተባለ ጀርመናዊ ክብ የሆነ ዲስክን በስፓይራል በምብሳት ይህ ዲስክ በተሽከረከረ ቁጥር ከፊትለፊቱ የሚመጣውን ብርሃን በቀዳዶቹ በማሾለክ ከሴሌኒይም በተሰራ የ ካሜራ ግድግዳ ላይ እንዲያርፍ አደረገ። ግድግዳው ብርሃን ሲነካው ያንን ብርሃን ወደ ኮሬንቲ ሃይል በመቀየር ምስልን በኮሬንቲ መልክ በሽቦ ለመላክ ቻለ። ነገር ግን በዚህ ጊዜ አምፕሊፋየር ስላልነበር የሚላከው ምስል እምብዛም አመርቂ አልነበረም።

ከ27 አመታት በኋላ በ1911 እ.ኤ.አ. የራሻው ቦሪስ ሮዚንግ ለመጀመሪያ ጊዜ የ ሲርቲን ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ አሁንም ለመጀመሪያ ጊዜ ተንቀሳቃሽ ምስልን ለመላክና ለመቀብል ቻለ። ነገር ግን የሚንቀሳቀሱት ምስሎች የጂዎሜትሪ ቅርጽ ነበራቸው ማለትም ሶስት ማዕዘን፣ አራት ማእዘን ወዘተ...

ከ7 አመታት በኋላ በ1925 እ.ኤ.አ. ጆን ሎጂ ቤርድ የተሰኘው የስኮትላንድ ተመራማሪ 2ቅጥ ያላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመላክ ቻለ ከዚያም በ1926 እ.ኤ.አ. ጥቁርና ነጭ የሆኑ ምስሎችን ለማስተላለፍ በቃ። በዚህ ጊዜ የሚላኩት ምስል ጥራት 30 መስመር በአንድ ጊዜ ነበር፣ በዚህም ምክንያት የሰውን ፊት ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ግን ይቻል ነበር። አቶ ቤርድ በጥር 18 ቀን 1918 ዓ.ም. (26 January 1926 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የቴሌቪዥን መግለጫ ሰጠ።

የቴሌቭዥን ብዛት በየ1000 ሰው በየአገሩ
  500–1000
  300–500
  200–300
  100–200
  50–100
  0–50
  No data

1927 እ.ኤ.አ. ኸርበርት አይቭስ የተሰኘው የ ቤል ላብራቷር ተቀጣሪ 16 የምስል ገጽታ በሰከንድ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኒውዮርክ ከተማ በሽቦ መላክ ቻለ። ቀጠል አድርጎም በራዲዮ ወደ ዊፓኒ ኒው ጀርሲ ለመላክ በቃ። በዚያው አመት ፊሎ ፍራንስዎርዝ የመጀመሪያውን የተሟላና በኤሌክትሪክ ስካኒንግ ብቻ የሚስራውን የቴሌቭዥን ስርዓት በተግባር አዋለ።.በጥር 1928 እ.ኤ.አ. (1920 ዓም) መጀመርያው የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያ በ ስከነክተዲ፣ ኒው ዮርክ ተከፈተ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ያሰራጫል።

በርግጥም የመጀመሪያው በሰፊው ተግባራዊ የሆነ የቴሌቭዥን ስርዓት ስራ ላይ የዋለው በጀርመን አገር ሲሆን ይኸውም በ1929 እ.ኤ.አ. ነው። በ1936 እ.ኤ.አ. (1928 ዓም) ጀርመን ሃገር ተደርጎ የነበረውን የ ኦሎምፒክ ውድድር በቴሌቭዥን ሊሰራጭ ቻለ፣ ህዝቡም ውድድሩን እቤቱ ሆኖ ቀጥታ ሲካሄድ ለማየት ቻለ።

ከዚያ መጀመርያው ጥቁርና-ነጭ ፕሮግራሚንግ በዩናይትድ ኪንግደም 1928 ዓም፤ በአሜሪካ 1933 ዓም ተደረገ። በአፍሪካ መጀመርያው ጣቢያዎች በ1952 ዓም በናይጄሪያና ደቡብ ሮዴዝያ (አሁን ዚምባብዌ) ተሰራጩ፣ በኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ስርጭት አገልግሎት (ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን) የጀመረው በ1956 ዓም ሆነ።

ሁለት አገራት - እነርሱም ቱቫሉኪሪባስ - ምንም የራሳቸውን ቴሌቪዥን አሁን አያሰራጩም፤ ሆኖም የሌላ አገር ስርጭት እዚያ ሊታይ ይችላል።

ከለር ቴሌቪዥን

ከዚያ ቤርድ በግንቦት 26 ቀን 1920 (ጁላይ 3, 1928 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የከለር ቴሌቪዥን ስርጨት ሙከራ አደረገ።

ነገር ግን ከለር ቴሌቪዥን ቢፈጠረም ለሚከተሉት ብዙ ዓመታት ስርጭት ባብዛኛው ጥቁርና ነጭ ብቻ ሆኖ ቀረ። ይሄው ቴክኖዎሎጂው በጣም ውድ፣ በጣም ከባድና በትክክል ያልተስተካከለ ስለ ሆነ ነው። በየጥቂቱ ከ1946 ዓም (1954 እ.ኤ.አ.) ጀምሮ አገራት ወደ ከለር ስርጭትና ከለሩን ማሳየት የሚችል ቴሌቪዥን ወደ መሸጥ ይዛወሩ ጀመር። በጥር ወር 1946 ዓም NBC የተባለው አሜሪካዊ ስርጭት ጣቢያ በከፊሉ ወደ ከለር ተሸጋገረ፤ ብዙ ሰዎች ግን ያንጊዜ ከለር ማሳያ ቴሌቪዥን ለመግዛት ገና አልቻሉም ነበር። ከ1955 እስከ 1959 ዓም ድረስ ሌሎቹ ትልልቅ አሜሪካዊ ጣቢያዎች ABC እና CBS ደግሞ ወደ ከለር ተዛወሩ፣ የከለርም ተቀባዮች ዋጋ እየተቀነሰ የሚይዩት ሕዝብ ቁጥር ደግሞ ከዚህ በኋላ እየተጨመረ ሄደ፤ ከረጅሙ ጥቁርና-ነጭ ዘመን ቀጥሎ ከለርም በኅብረተሠብ ያመጣው ለውጥ ለግዙፍነቱ በኋላ ኢንተርኔት እንደ ሆነ ያሕል ነው።

ጃፓን1952 ዓም፣ ሜክሲኮ በ1955፤ ካናዳ1958፣ የአውሮፓ ኅብረትየሶቪዬት ሕብረት በ1959፣ ኮት ዲቯር በ1962፣ አውስትራሊያ1967 ከለር ስርጭትን ጀመሩ። በኢትዮጵያም ከለር ስርጭት ከ 1976 ዓም ጀምሮ ተገኝቷል። በ 1977 ዓም ሮማኒያ ከጥቁርና-ነጭ ስርጭት ወደ ከለር ማሰራጨት የለወጠ በዓለም መጨረሻው ሃገር ሆነ።

Other Languages
Afrikaans: Televisie
Alemannisch: Fernsehen
aragonés: Televisión
Ænglisc: Feorrsīen
العربية: تلفاز
ܐܪܡܝܐ: ܦܪܣ ܚܙܘܐ
অসমীয়া: দূৰদৰ্শন
asturianu: Televisión
azərbaycanca: Televiziya
تۆرکجه: تلویزیون
башҡортса: Телевидение
žemaitėška: Televėzėjė
беларуская: Тэлебачанне
беларуская (тарашкевіца)‎: Тэлебачаньне
български: Телевизия
भोजपुरी: टेलीविजन
বাংলা: টেলিভিশন
brezhoneg: Skinwel
bosanski: Televizija
буряад: Телевиз
català: Televisió
Mìng-dĕ̤ng-ngṳ̄: Diêng-sê
qırımtatarca: Telekörüv
čeština: Televize
kaszëbsczi: Telewizjô
Чӑвашла: Телекурăм
Cymraeg: Teledu
dansk: Fjernsyn
Deutsch: Fernsehen
Thuɔŋjäŋ: Atoockïït
Zazaki: Têlevizyon
Ελληνικά: Τηλεόραση
emiliàn e rumagnòl: Televisiån
English: Television
Esperanto: Televido
español: Televisión
euskara: Telebista
estremeñu: Televisión
فارسی: تلویزیون
suomi: Televisio
Na Vosa Vakaviti: Television
føroyskt: Sjónvarp
français: Télévision
arpetan: Tèlèvision
Frysk: Telefyzje
Gaeilge: Teilifís
贛語: 電視
Gàidhlig: Telebhisean
galego: Televisión
Avañe'ẽ: Ta'ãngambyry
गोंयची कोंकणी / Gõychi Konknni: दूरचित्रवाणी
Bahasa Hulontalo: Televisi
Hausa: Talabijin
客家語/Hak-kâ-ngî: Thien-sṳ
Hawaiʻi: Kelewikiona
עברית: טלוויזיה
हिन्दी: दूरदर्शन
Fiji Hindi: Television
hrvatski: Televizija
Kreyòl ayisyen: Televizyon
magyar: Televízió
interlingua: Television
Bahasa Indonesia: Televisi
Iñupiak: Taġġiraun
Ilokano: Telebision
íslenska: Sjónvarp
italiano: Televisione
日本語: テレビ
Patois: Telivijan
Basa Jawa: Télévisi
ქართული: ტელევიზია
Taqbaylit: Tiliẓri
Kabɩyɛ: Televiziyɔɔ
Gĩkũyũ: Terebiceni
қазақша: Телевидение
ភាសាខ្មែរ: ទូរទស្សន៍
ಕನ್ನಡ: ದೂರದರ್ಶನ
한국어: 텔레비전
कॉशुर / کٲشُر: ٹٮ۪لِوِجَن
kurdî: Televîzyon
Кыргызча: Телекөрсөтүү
Latina: Televisio
Ladino: Televizyón
Lëtzebuergesch: Televisioun
Lingua Franca Nova: Televisa
Limburgs: Tillevies
Ligure: Televixon
lumbaart: Television
lietuvių: Televizija
latviešu: Televīzija
मैथिली: टेलिभिजन
Basa Banyumasan: Televisi
Malagasy: Televiziona
македонски: Телевизија
മലയാളം: ടെലിവിഷൻ
монгол: Телевиз
Bahasa Melayu: Televisyen
Mirandés: Telbison
မြန်မာဘာသာ: တယ်လီဗစ်ရှင်း
مازِرونی: تیلوزیون
Plattdüütsch: Feernseher
Nedersaksies: Televisy
नेपाली: टेलिभिजन
नेपाल भाषा: टेलेभिजन
Nederlands: Televisie
norsk nynorsk: Fjernsyn
norsk: Fjernsyn
Novial: Televisione
Nouormand: Télévision
occitan: Television
ਪੰਜਾਬੀ: ਟੈਲੀਵਿਜ਼ਨ
Papiamentu: Television
Picard: Télévision
Deitsch: Guckbax
polski: Telewizja
پنجابی: ٹیلیوژن
پښتو: تلويزون
português: Televisão
Runa Simi: Ñawikaruy
română: Televiziune
русский: Телевидение
русиньскый: Телевізія
संस्कृतम्: दूरदर्शनम्
саха тыла: Телевидение
ᱥᱟᱱᱛᱟᱲᱤ: ᱧᱮᱱᱮᱞᱚᱢ
sicilianu: Televisioni
srpskohrvatski / српскохрватски: Televizija
slovenčina: Televízia (prenos)
slovenščina: Televizija
Gagana Samoa: Televise
Soomaaliga: Telefishin
српски / srpski: Телевизија
Seeltersk: Fiersjoon
Basa Sunda: Televisi
svenska: Television
Kiswahili: Televisheni
ślůnski: Telewizyjo
తెలుగు: టెలివిజన్
тоҷикӣ: Телевизион
ትግርኛ: ቲቪ
Türkmençe: Telewizor
Tagalog: Telebisyon
Türkçe: Televizyon
татарча/tatarça: Телевидение
ئۇيغۇرچە / Uyghurche: تېلېۋىزور
українська: Телебачення
oʻzbekcha/ўзбекча: Televideniye
vèneto: Tełevixion
Tiếng Việt: Truyền hình
walon: Televuzion
Winaray: Telebisyon
吴语: 电视机
მარგალური: ტელევიზია
ייִדיש: טעלעוויזיע
Yorùbá: Tẹlifísàn
Zeêuws: Tillevisie
中文: 电视
文言: 電視
Bân-lâm-gú: Tiān-sī
粵語: 電視