ሥነ ግራፍ
English: Graph theory

የግራፍ ምስል

ሥነ ግራፍሒሳብ ትምህርት አካል ሲሆን የሚያጠናውም ግራፍ የሚሰኙ የሒሳብ መዋቅሮችን ነው። እዚህ ላይ ግራፍ ሲባል የሁለት ጥንድ ነገሮችን ዝምድና የሚወክል ጽንሰ ሐሳብ ነው። ግራፍ እንግዲህ የጉብሮችና ጉብሮችን የሚያገናኙ ጠርዞች ስብስብ ነው። ሁም ግራፎች በሁለት ይከፈላሉ፣ እነርሱም አቅጣጫዊ እና ኢአቅጣጫዊ ናቸው። ኢአቅጣጫዊ እሚባለው በአንድ ጠርዝ ላይ ያሉ ሁለቱ ጉብሮች አንዳቸውን ከሌላው የሚለያቸው ነገር ሳይኖር ሲቀር ነው። ለምሳሌ ሁለት ሰዎች ቢጨባበጡ፤ ሰውየ ሐ ሰውየ መ ን መጨበጡ ሰውየ መ ሰወየ ሐን ከመጨበጡ ጋር ምንም ልዩነት የለውም ።ስለሆነም ሐ ና መን እንደጉብር ብንወስድና መጨባበጣቸውን እንደ ጠርዝ ብንስል፤ የምናገኘው ግራፍ ኢአቅጣጫዊ ይሰኛል ማለት ነው።በዚህ ተቃራኒ አቅጣጫዊ ግራፍ ሁለቱን ጉብሮች ይለያል። ስለዚህም ግራፉ ከአንዱ ጉብር ወደ ሌላው የተሰነዘረ ነው እንላለን። ለምሳሌ በአንድ ድግስ ውስጥ አበበን መሰረት ብታውቀው፤ የርሷ እርሱን ማወቅ የግዴታ እርሱ እሷን ያውቃታል ማለት አይደለም። ስለሆነም ግራፉ ከመሰረት ወደ አበበ ይተሰነዘረ አቅጣጫዊ ግራፍ ነው እንላለን።

Other Languages
беларуская: Тэорыя графаў
čeština: Teorie grafů
dansk: Grafteori
Ελληνικά: Θεωρία γράφων
English: Graph theory
Esperanto: Grafeteorio
euskara: Grafo teoria
Bahasa Indonesia: Teori graf
íslenska: Netafræði
日本語: グラフ理論
한국어: 그래프 이론
lietuvių: Grafų teorija
latviešu: Grafu teorija
монгол: Графын онол
Bahasa Melayu: Teori graf
Nederlands: Grafentheorie
norsk nynorsk: Grafteori
norsk: Grafteori
português: Teoria dos grafos
sicilianu: Tiuria dî grafi
srpskohrvatski / српскохрватски: Teorija grafova
Simple English: Graph theory
slovenčina: Teória grafov
slovenščina: Teorija grafov
српски / srpski: Теорија графова
svenska: Grafteori
Türkçe: Çizge teorisi
українська: Теорія графів
Tiếng Việt: Lý thuyết đồ thị
吴语: 图论
中文: 图论
粵語: 圖論